Home የመሰናዶ ት/ ቤት ተማሪዎች ኮሌጃችንን ጎበኙ

የመሰናዶ ት/ ቤት ተማሪዎች ኮሌጃችንን ጎበኙ

17th June, 2024

ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ ቤት ተማሪዎች ኮሌጃችንን ጎበኙ።
ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከተለያዩ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን መጎብኘታቸው ለመወቅ ተችሏል።
በጉብኝቱም ፊትአውራሪ ላቀው አዲገህ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት፣ ለቡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ላፍቶ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት እና አየር አምባ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ተማሪዎች ተሳትፋዋል። ለጎብኚዎች የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አካደሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይራረክተር እና ሠልጣኝ ልማት ም/ል ዲን ወ/ሮ ዋጋዬ ገ/መድን ስለ ቴክኒክና ሙያ እና ስለ ንፋስ ስል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አጭር ገለፃ ካደራጉላቸው ቦኃላ የኮሌጁን የተለያዩ ወርክ ሾፖችን እንድጎብኙ ተደርጓል።
በሌላ ዜና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሠልጣኞች በኮሌጃችን መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጣና ወስደው ላጠናቀቁት ሠርትፊኬት የማስጠት ሥና ሥርዓት በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲኒማ አደራሽ ተከናወነ። በፕሮግራሙ ላይ የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ኢ/ር ደነቀ ደሣለኝ ኮሌጅን ወክለው የምስክር ወረቀት/Certificate አስረክበዋል።ለሠልጣኞች በስተላለፉት መልዕክት ሥልጣነውን ወደ ተግባር ቀይረው ራሳቸውንና ሃገራቸውን እንድለወጡ አሳስበዋል። ሠልጣኞች በበኩላቸው ኮሌጁ ስላደረጋላቸው ቀና ትብብር ከልብ አመስግነው ሥልጣናውን ወደ ተግባር እንደምለውጡ ለማወቅ ተችሏል።
.

Copyright © All rights reserved.